ራዕይ፡-
ጎጃም የበለፀገ ሕዝብ መኖሪያ እና በኢትዮጵያ የተስፋ ምድር ሆኖ ማየት፡፡
ተልዕኮ ፡-
በጎጃም የተለያዩ ወረዳዎች የሚሠሩ የልማት ሥራዎች የማኅበሩን ዓላማዎችና
መንግሥት የሚያወጣቸውን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ ሥርዓት ባለው
አደረጃጀት እየተመሩ የሚከተሉትን ማከናወን፡-

  1. የሕዝቡን አቅም ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በአካባቢው የሚታቀዱ ሥራዎችን
    መመጠንና የሕብረተሰቡን ተሳትፎ በማስፋት ተግባራዊ ማድረግ፡፡
  2. በአካባቢ ጥበቃ ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ መሥራት፣
  3. በማሕበራዊ ዘርፍ በሚካተቱት በትምህርት፣ በጤና፣ በመሠረተ-ልማት
    ዘርፎችና በመሳሰሉት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት፣
  4. በባሕላዊና ቅርስ ጥበቃ ዘርፎች አካባቢውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ
    ጥረት ማድረግ፣
  5. በሌሎች ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሥራዎች ከሚሠሩ ድርጅቶች ጋር
    በጋራ መሥራት፣
Scroll to Top