ራዕይ፡-
ጎጃም የበለፀገ ሕዝብ መኖሪያ እና በኢትዮጵያ የተስፋ ምድር ሆኖ ማየት፡፡
ተልዕኮ ፡-
በጎጃም የተለያዩ ወረዳዎች የሚሠሩ የልማት ሥራዎች የማኅበሩን ዓላማዎችና
መንግሥት የሚያወጣቸውን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ ሥርዓት ባለው
አደረጃጀት እየተመሩ የሚከተሉትን ማከናወን፡-
- የሕዝቡን አቅም ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በአካባቢው የሚታቀዱ ሥራዎችን
መመጠንና የሕብረተሰቡን ተሳትፎ በማስፋት ተግባራዊ ማድረግ፡፡ - በአካባቢ ጥበቃ ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ መሥራት፣
- በማሕበራዊ ዘርፍ በሚካተቱት በትምህርት፣ በጤና፣ በመሠረተ-ልማት
ዘርፎችና በመሳሰሉት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት፣ - በባሕላዊና ቅርስ ጥበቃ ዘርፎች አካባቢውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ
ጥረት ማድረግ፣ - በሌሎች ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሥራዎች ከሚሠሩ ድርጅቶች ጋር
በጋራ መሥራት፣