ጎጃም በሰሜን ምራብ ኢትዮጵያ የሚገኝና በአባይ ወንዝ ተከቦ የሚገኝ ባህር ዳር፣ ፍኖተ ሰላም(ቆላ-ደጋዳሞት) ፣ አገው ምድር፣ መተከል ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ሞጣና ብቸና አውርጃዎች እና በነዚ ውስጥም ከ 35 በላይ ወረዳዎችን ይዞ የሚገኝ የራሱ መንግሥት የነበረው ከፍለ-ሃገር ነው። ጎጃም እንደነ በላይ ዘለቀ ያሉ ጀግኖች መፈጠሪያ እንዲሁም የ አባይ እና የጣና ባለቤት ናት ፡፡
ጎጃም የቅኔ ትምህርት በስፋት የሚሰጥበት ፡እንዲሁም እንደነ የፍቅር እስከ መቃብር ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ (ዶ ር) (1902- 1996 )ዓ.ም አቤ ጉበኛ (1925 – 1972 )ዓ.ም ዮፍታሄ ንጉሤ(1897-1937 ) ዓ.ም የመሳሰሉ የጥበብ ሰወችን አፍርታለች ፡፡ ጎጃም በጤፍ አምራችነት ከታወቁት የኢትዮጵያ ክልሎች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። በተለይ የአዴት ጤፍ በባህር ዳር ጎንደር ደሴ እና መቀሌ ነዋሪዎች ዘንድ በስፋት የታወቀ እና ተወዳጅም ነው። እንዲሁም በምስራቅ ጎጃም እነብሴ ሞጣ ዙሪያ ወይንውሀ እና ጎንቻ ሲሶ ግንደወይን ዙሪያ የሚመረተው ጤፍ የአዲስ አበባን ህዝብ ገትሮ እንደያዘ ይነገራል።[[ቡሬ]] ዙሪያ የሚበቅለው በርበሬ በቆሎ ደግሞ የመላው የኢቲዮጵያን ህዝብ ገትሮ እንደያዘም ይነገርለታል፡፡ በነገራችን ላይ ቡሬ ዙሪያ ይህንን ብቻ አይደለም የሚያበቅል እንደ ጤፍ፣ሽንብራ፣ቦለቄ፣ዳጉሳ፣መጥቀስ ሆነብን እንጂ የማይበቅል ነገር የለም፡፡በዋናነትም ከ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ [[ገዳም ልጃሞር]] ቀበሌ ይህንን በማምረት ይጠቀሳል፡፡ ጎጃም ሌሎች እንደ ገብስ ስንዴ በቆሎ ባቄላ አተር ወዘተ የሰብል አይነቶችን በማምረትም ይታወቃል። ጎጃም የአባይ እና ሌሎች የበርካታ ወንዞች መነሻ ነው ።ጮቄ ተራራ በዚሁ ክፍለ ሃገር ይገኛል።ጎጃም በኣሁኑ ጊዜ ማለትም ኣገራችን የፌደራሊዝም ስርኣት ከተከተለች ወዲህ ከኣራት ኣስተዳደር ዞን ተከፍሏል ።ሶስቱ ማለትም አዊ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም በአማራ ክልል ሲገኙ መተከል ቤሻንጉል ጉምዝ ክልል ተካቷል ።
ጎጃም አመቺ የአየር ንብረት፣ ለም አፈርና ዓባይን ጨምሮ በርካታ ታላላቅ ወንዞች የሚፈሱበት በተፈጥሮ የታደለ አካባቢ ነው፡፡
ሕዝቡም ጠንካራና ታታሪ ሠራተኛ ነው፡፡ ይሁንና በዘመናት የሕይወት ተሞክሮ የዳበረውን አካባቢያዊ ዕውቀት (Indigenous knowledge) ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር አጣጥሞና ሕዝቡን አስተባብሮ ወደ ዕድገት ሊያመራ የሚችል አሳታፊ የልማት ስትራቴጂ ተግባር ላይ ሊውል ባለመቻሉ የአካባቢው ሕዝብ እንደሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ሁሉ ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋልጦ ይገኛል፡፡
ባሳለፍናቸው ጥቂት ዓመታት የተፈጠሩ ምቹ አጋጣሚዎች ተጠቅሞ ይህን ችግሩን ደረጃ በደረጃ ለማቃለል መንግሥት እያደረገ ያለውን ጥረት ማገዝ ከተወላጆችና ደጋፊዎች ሁሉ የሚጠበቅ በጎ ተግባር መሆኑም ይታመናል፡፡ ይህንኑ ሀሳብ መነሻ በማድረግ በአካባቢው ልዩ ልዩ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳትፎ ለማድረግ ታስቦ የጎጃም ልማት ማኅበር ተመሰረተ