






-
በጎጃም እጅግ ከፍተኛ ሥራ የሠሩና ዘመናዊ ትምህርት እንዲስፋፋ ያደረጉ ‹‹የዘመናዊ ትምህርት አባት›› እየተባሉ በሚጠሩት በአቶ በትረፅድቅ ካሣ ስም የጎጃም ልማት ማኅበር ስኮላርሺፕ አቋቁሞ ሥራውን ከጀመረበት ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ዝግጅታቸውና ውጤታቸው ከፍተኛ የሆኑ ከ10ኛ ክፍል ወደ መሰናዶ ት/ቤት ሲገቡ ( 11ኛ ክፍል ሲያልፉ) በ1998 ዓ.ም በ100 ተማሪዎች ድጋፍ ማድረግ ጀምሮ እስከ 2015 የትምህር ዘመን መጨረሻ ድረስ ከተለያዩ 192 ከሚሆኑ የሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤቶች የተመረጡ 3100 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ከ2300 በላይ የሚሆኑት ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በተለያዩ ደረጃዎች (በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በሶስተኛ ዲግሪ) ተመርቀዋል፡፡

-
በጎጃም በተለያዩ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች 7 የችግኝ ማዘጋጃ ቦታዎችን በመረከብ ከየወረዳው ግብርና ልማት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የተጀመረው የችግኝ ማዘጋጀት ሥራ ተከናውኖ 57 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ተዘጋጅተው ለገበሬዎች የተከፋፈሉ ሲሆን የደን ቦታዎችም ተመርጠው የተከላ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
-
ጎጃም እጅግ ብዙ ቅርሶች ያሉበት አካባቢ መሆኑን ለመረዳት ሰፊ ጥናትን
የሚጠይቅ አይደለም፡፡ በእየ አጥቢያውና ቀበሌው የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት
ጥንታዊ ንዋየ ቅድሳት፣ ገዳማትና ሐይቆች፣ ተራሮችና ሸለቆዎችን መፈተሽ በቂ
ነው፡፡
የጎጃም ልማት ማኅበር ድጋፍ ያደረገ አባላቱም የበኩላቸውን የጥናት ሥራዎችን ያደረጉት ለመርጦለ ማርያም ገዳም ብቻ ነው፡፡ ይህም ገዳሙ ካለበት ሁኔታ የበለጠ ጉዳት እንዳያጋጥመው በፀሐይና ዝናብ የበለጠ እንዳይጎዳ ለተደረገው ከፀሐይና ዝናብ ለመከላከል የአቅሙን ለማድረግ ችሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በባለሙያዎች ሰፊ ጥናት ተደርጎ በቀጣይነት ለሚሠሩ ሥራዎች በጀት የማፈላለግና በዩኔስኮ በቅርስነት እንዲመዘገብ ለማድረግ ጥረት አድርገዋል፡፡ በሌሎች እጅግ ጥንታዊ ገዳማት ተመሳሳይና ዘላቂነት ያላቸው ሥራዎችን መሥራት አስፈላጊ ነው፡፡











